Month: May 2017

 • የአጭር ልብወለድ ታሪክ

  የአጭር ልብወለድ ታሪክ

  ‘አሞራና ቅል ተጋቡ። ቅሉ ተሰበረ። አሞራውም በረረ።’ … አጭር ልብወለድ ታሪክ ልክ እንደዚህ እጥር፣ ምጥን፣ ጣፈጥ ማለት አለበት።

 • “ጅብ ነች” (ልብወለድ)

  “ጅብ ነች” (ልብወለድ)

  “ልጄ እንግዲህ ትሰማ እንደሆነ የወለድኩህ እኔ ነኝ አንተ አይደለህም ስማኝ! ጅብ ትሆናለች ስልህ ጅብ ትሆናለች ነው። ይህን የአንተን አትሆንም የሚለውን መጽሐፍ ለዚያው ላዲስ አበባህ አድርገው!”

 • ማኅደረ ብርሃን – ሀገረ ጃፓን

  ማኅደረ ብርሃን – ሀገረ ጃፓን

  ቀሚሱን እስከ እግር ጣቱ ሰዶ ወንዱንም ሴቱንም በቶኪዩ ጐዳና ድምቡል ድምቡል ሲል ያሳዩሃል። እንዲህ አስተዋውቀውህ ከቤቱ ሲወስዱህ ተንበርክኮ ይቆይሃል፤ “ንበር ሊለኝ ነው ሊነሳልኝ ነው” ስትል ፍግም ብሎ መሬት ይስምልሃል። አደግድግ አንተም … እንዳገርህ ‘ክበር ተከባበር’ ነውና እጅ ንሳ።

 • የጃፓን ባህል ቅኝት

  የጃፓን ባህል ቅኝት

  የካቲት 3 ቀን በጃፓን የክረምት ማጋመሻ በዓል ይባላል። በዚህም በዓል ቤተ ዘመዱ ሁሉ በየቤቱ እየተሰበሰበ ቆሎ እየተቆላ ‘ሰይጣንና ክፉ ነገር ውጣ … ሲሳይና ጤና ወደ ቤት ግባ’ እያለ ቆሎውን እየዘገነ ይበትናል፤ የተረፈውንም ይበሉታል። ይኸውም ባገራችን በኢትዮጵያ በየባላገሩ ለእንቁጣጣሽና ለግንቦት ልደታ እንደሚደረገው ነው።

 • ግስ ዘመምህር ክፍሌ

  ግስ ዘመምህር ክፍሌ

  አለቃ ኪዳነ ወልድ እንደሚሉት መምህር ክፍለ ጊዮርጊስን ለመዝገበ ቃላት ሥራ ያነሳሳቸው የዲልማን መጽሐፍ ነው። ሆኖም የመምህር ክፍሌ ግስ በቃላት አመራረጥና አፈታት እንዲሁም በጥቅስ ምርጫው የራሱን መንገድ የቀየሰ ይመስላል።

 • “ጉባኤው” (ልብወለድ)

  “ጉባኤው” (ልብወለድ)

  መሪጌታ ስነ ኢየሱስ ብድግ ብለው ጃንሆይን ሽቅብ እየተመለከቱ፣ “ወንድሜ ነጋድራስ የተከበረውን ቋንቋችንን ሲዘነጣጥለው ባይ እንባዬ መጣ! … በመዠመሪያ ጅረት ማለት ሲገባው አናሳ ወንዝ አለን። ዝም አልነው። ቀጥዬ ማለት ሲገባው ለጥቄ ብሎ ተናገረ … እንግዲህ ይህን ዝም ብሎ ማለፍ እንደምን ይቻላል?”

 • መምህር ክፍለ ጊዮርጊስ (፲፰፻፲፯-፲፱፻)

  መምህር ክፍለ ጊዮርጊስ (፲፰፻፲፯-፲፱፻)

  ሮሜ ሄጄ ከፈረንጅ ሊቃውንት ሁሉ በእውቀት የሚበልጥ፣ ቋንቋ ዐዋቂ ሰው አገኘሁ። ይህም ሰው፣ ‘ኢትዮጵያዊ ሊቅ ሆይ! ግእዝና አማርኛ አስተምረኝ፣ እኔም የፈለግከውን አስተምርሃለሁ’ አለኝ።