“ሳይቸግር ጤፍ ብድር” (ወግ)

“ሳይቸግር ጤፍ ብድር”

ከሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው

.

አንድ ሰሞን ሰባት ገጽ ከሩብ የኾነ የአንድ ሥራ-ሀላፊን ያማርኛ ጥያቄና መልስ (ቃለመጠይቅ) ጽሑፍ አንብቤ ነበር። ሃያ ሦስት የእንግሊዝኛ ቃላት/ሐረጎች ተቀላቅለውበት አገኘሁ! ይህ የጽሑፉ 1.06% መሆኑ ነው።

ታዲያ “ይቺ ምን አላትና ሰው ታስተቻለች?” ያሰኝ ይሆናል።

ጉዳዩ ግን መጠኑ አይደለም – ሌላ ነው። አንደኛ፣ ሰው ሀላፊ ኾኖ ባደባባይ ንግግሩ እንግሊዝኛን ካማርኛ እያቃየጠ ሲናገር ላድማጮቹ ኹሉ አብነት ይኾናል። ኹለተኛ፣ አቀያይጦቱ “ሳይቸግር ጤፍ ብድር” መሆኑ ነው።

ቀጥዬ ከጽሑፉ የለቀምኩዋቸውን አማርኛና-እንግሊዝኛ ቅይጥይጥ ንግግር አመጣለሁ።

.

ቅይጡ ቃል                በጽሑፉ ያለው አጠቃቀም       (በጎ የሚሆነው)

Albergo             “አንድ ቦታ ነበር ቤርጎ የያዝነው”   (አንድ ቦታ ነበር ሆቴል የያዝነው)

Already              “ኦረዲ ወስነናል”   (ዱሮ ወስነናል)

Chair                  “ቸር ማድረጉንም”   (ስብሰባውን መምራቱንም)

Chairperson       “ለዋናው ቸርፐርሰን”   (ለዋናው ሊቀመንበር)

Cross-check            “ይህንኑ ክሮስቼክ አደረግን”   (ይህንኑ አመሳከርን)

Excessive Force         “ይህ ኤክሴሲቭ ፎርስ ነው”   (ይህ መጠኔለሽ ኃይል ነው)

Extension                  “ለምን ኤክስቴንሽን አይጠይቁም”   (ለምን የጊዜ ተራዝሞ አይጠይቁም)

Information               “ኢንፎርሜሽን በሚስጥር እያወጣ”   (መረጃ በሚስጥር እያወጣ)

Interrogate                “ኢንተሮጌት አድርጓቸዋል”   (እሳቸውንም ጠይቋቸዋል)

I Think                       “አይቲንክ”   (ይመስለኛል)

Leads                         “የካሴት ሊዶችን ለማትረፍ”   (የካሴት መረጃዎችን ለማትረፍ)

Legal Adviser         “ሌጋል አድቫይዘር በመሆን”   (የሕግ አማካሪ በመሆን)

Organization          “ከማንም ኦርጋናይዜሽን ጋር”   (ከማንም ድርጅት ጋር)

Pressure                  “ፕሬዠሩን በመፍራት”   (ጫናውን በመፍራት)

Property Damage        “የደረሰባቸውን የፕሮፐርቲ ዳሜጅ”   (የደረሰባቸውን የሀብት ጥፋት)

Region                     “የደቡብ ሪጅን”   (የደቡብ ቀጣና/ክፍለ ሀገር)

Replace                    “በሕጉ ምክትሉ ሪፕሌስ ያደርጋል”   (በሕጉ ምክትሉ ይተካል)

Report                     “የናንተን ውሳኔ ሪፖርት”   (የናንተን ውሳኔ ዘገባ)

Resign                      “አንዱ ሪዛይን አድርጎ”   (አንዱ ሥራውን ለቆ)

Scholarship             “እስኮላርሺፕ አግኝቶ ነው”   (የትምህርት ድጎማ አግኝቶ ነው)

Statement                “የራሴን ስቴትመንት ሳደርግ”   (የራሴን ቃል ስሰጥ)

Supreme Court       “ሱፕሪም ኮርት ቢሮ ስንደርስ”   (ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢሮ ስንደርስ)

Trust                         “ትረስት ለማድረግ ሞክረን”   (ለማመን ሞክረን)

.

እዚህ ላይ በተጠቅሞቴ (ለምሳሌ) Albergoን “ሆቴል” ብያለሁ። በፈረንጅኛነቱ በቅየማ ሊያስከስስ ይችላል። ይህ ቃል ግን አማርኛ ኾኑዋል።

ለምሳሌ “Apple” ባማርኛ ምንድን ነው ተብሎ ቢጠየቅ ማንም “ፖም” ይላል – ከፈረንሳይኛ በመጣ ቃል። በዚህ መልክ ብዙ የውጭ ቃላት ወደ አማርኛ መጥተው፣ በዘመን ብዛት አማርኛ የኾኑ አሉ – ሆቴልም የዚያ ዐይነት ነው።

ከላይ የተዘረዘሩት የሃያ ሦስቱ ፈረንጅኛ ቃላት/ሐረጎች ጉዳይ ግን ሌላ ነው … ሀሳባቸው በአማርኛ በቀላሉ ይገኛልና።

.

ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው

(1999 ዓ.ም)

.

[ምንጭ] – አንድምታ ክበብ። ቁጥር 6። የካቲት 1999። ገጽ 8።

 

2 thoughts on ““ሳይቸግር ጤፍ ብድር” (ወግ)

 1. ይኸ ባለፈው ወር ከሕይወት ታደሰ ጋር ካደረጋችሁት ቃለ-ምልልስ ውስጥ የተገኘ ነው። የእንግሊዝኛ ቃላት የተቀጠሉት የአማርኛው በቂ ስላልሆነ እንዳይደለ እናስተውል!
  ትረካ (story telling)
  የገዳመ ሲታውያን ማርያም ጽዮን ትምህርት ቤት (Cistercian Monastery Mariam Tsion School)
  በጸሎት በምንጀምርበት አዳራሽ (ቻፕል)
  ኪነጥበባዊ ፍላጎት (interest)
  ሁሉን ጠለቅ (pervasive)
  የተጻፈበት ዘመን መንፈስ (Zeitge[i]st)
  የአነጋገር ዘዬ (accent)
  ለጊዜውና ለቦታው እውነተኛ (authentic)
  በጣም ዘመናዊ (modern)
  ዘመነኛ (contemporary)
  ከአሰራር ልማድ (routine)

  በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ማሰላሰልና መወያየት ይጠቅማል፤ 1/ በሚታተሙ ጽሑፎች ላይ የአርታኢ ኃላፊነት እስከምን ድረስ ነው? 2/ በቃለ-ምልልሶች ላይ ተቀላቅለው ለሚደመጡ የእንግሊዝኛ ቃላት ወዲያው ፍቺ ወይም ማብራሪያ የመስጠት አስፈላጊነትስ? 3/ የተማረው ክፍል በአማርኛ ሲነጋገር እንግሊዝኛ እንጂ አገር-በቀል [ኦሮምኛ ወይም ሲዳምኛ ወዘተ] የማይቀላቅለው ለምንድነው? 4/ እንግሊዝኛ አንባቢው [ፊደል የቆጠረው ወገን] የትኞቹን አስተሳሰቦች ሳያብላላ በማስተላለፉ ለጉራማይሌ አስተሳሰቦች፣ አባባሎች፣ ልምዶች ምክንያት ሆነ? 5/ የአገር መሪዎች፣ መምህራን፣ ቤተ እምነቶች፣ መገናኛ ብዙሃን፣ ጸሐፍት፣ የንግድ ማዕከላት፣ የመንግሥት ጽህፈት ቤቶች፣ ወዘተ ከዚህ ልማድ እንዲታቀቡ ምን ይደረግ?

  Like

 2. My problem is that, wipes with my stress using native languages, the audience think as I am conservative. May be the interviewee problem is the same.

  Like

አስተያየት ለመስጠት

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s