“አሞራ … የዳዊት አሞራ” (ግጥም)

“አሞራ … የዳዊት አሞራ”

በዣን ተኵላ

.

[1400 ዓ.ም]

.

Dawit 1

Dawit 2

Dawit 3

Dawit 4

Dawit 5

Dawit 6

.

.

በዘመናችን አማርኛ …

(ትርጉምና አሰናኝ)

በዕውቀቱ ሥዩም

.

.

“አሞራ የዳዊት አሞራ

ተከተለኝ ከኋላ፤

.

ላቅርብልህ ሥጋ ብላ

ላጠጣህ ወይ ደም መራራ

ተከተለኝ እኔ ልምራ፤

.

እየመተርሁ በካራ

እየወጋሁ በጦር ጣምራ።

.

ብንበላብህ አደራ

በገላችን ጦር ይዘራ፤

ክንፍ አውጥተን ብንሸሽም

ቀስትህ ትውጋን ተወርውራ።

.

ምንም ሆድ ቢብሰን እኛ አንበላም መሐላ

ገላችን ይምሰል እንጂ የፈጠጋር አምባራ

አፋችን ይምሰል እንጂ ባልቴት ምትሞቀው እንሶስላ

ጣታችንም ይምሰል ጭራ የጎረሰ ደም አበላ፤

.

ጭፍሮች ነነ የዣን ተኵላ

እኛስ አንበላም መሐላ!”

.

.

.

[በ1400ዎቹ አማርኛ በድጋሚ]

.

“አሞራ የዳዊት አሞራ

ተኸተለኝ በኋላ፤

.

ሥጋ አበላኽ ሐበላ (ከበላ)

የደም አጠጣኽ ነተራ (መራራ)

ተኸተለኝ በኋላ፤

.

ወግዕቼ በቃራ (በካራ)

ሰኽቼ በጸመራ። (በጣምራ)

.

እኛስ ብንበልዓኽ መሐላ

ለጾር ይስጠን ለወርወራ፤ (ውርወራ)

የከንፍ ብናደርግ ጽላ

ለቀስት ይስጠን ለቀፈራ። (ለወጠራ)

.

ምን ከበአሰን ንበልአኹ መሐላ (እንበላለን)

ገላችን ከመሰል የፈጠጋር እምብላ (አምባር)

አፈችን ከመሰል በዓልቴት የገባች እንሶስላ

ፀዓታችን የመሰል በደም የዘራ ጭራ (ጣታችን)

.

ስማችን የዣን ተኵላ

አንበልዓም መሐላ። (አንበላም)

.

የዣን ተኩላ

[ከአፄ ዳዊት ሠራዊቶች የአንዱ ስም]

(1400ዎቹ)

.

[ምንጭ] – Ms Bruce 88። Oxford Bodleian Library። ቅጠል 37ሀ።

 

4 thoughts on ““አሞራ … የዳዊት አሞራ” (ግጥም)

  1. ግጠሙስ ሸጋ ነው!

    በ1400 እና በ200 ዓ.ም መካከል ያለው ቋንቋ እጅግ ከመለያየቱ የተነሳ የፊቱ ግጥም በሌላ ቋንቋ የተፃፈ ሁሉ መስሎኝ ነበር።

    Like

አስተያየት ለመስጠት