ስለመጽሔቷ

“አንድምታ”

ከአስርት ዓመታት በፊት በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ክበብ ስም “አንድምታ” የተሰኘች አንዲት የሥነጽሑፍ ልሳን እናዘጋጅ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አንድምታ አድጋ በሰፊው “ጥበብ” ላይ የምታተኩር መጽሔት ሆና ቀርባለች። በዚችም መጽሔት የሥነ ጽሑፍ፣ ኪነ ጥበብ፣ ሥነ ሕንጻ፣ ኪነ ባህል እና ተመሳሳይ የጥበብ ዘርፎችን ለማቅረብ ፍላጎታችን ነው፡፡

አንድም፣ ጥበባዊ እይታ ብዙ አይነት መልክ የሚይዝ ነውና፤ አንድም ደግሞ፣ ጥበብን ለመረዳት ዘርፈ ብዙ ጥናት ይጠይቃልና። 

እስከዛሬ፣ በምንወዳቸውና በማንጠግባቸው ሥራዎች ስንመሰጥ፣ “መቼ ይሆን የሀገራችን ድርሰቶች የሚገባቸውን ክብር የሚያገኙት?” እያልን መብከንከናችን አልቀረም። ይህም የሚቻለው አንባቢዎች ከበርካታ ሺዎች ወደ ጥቂት ሚልዮኖች መድረስ ሲችሉ ይመስለናል።

እናም (በአቅማችን) የአንባቢውን ቁጥር ለመጨመር ጥበብን በ“አንድምታ” ለማቅረብ ወሰንን።

ሕይወት ከተማ

ኅሩይ አብዱ

ብሩክ አብዱ

እንድርያስ ተክሉ

17 thoughts on “ስለመጽሔቷ

  1. ሠናይ ሐሳብ ነው በርቱ! ትውልድ ከሚቀረጽበትና ከሚታነጽባቸው መንገዶች አንዱና ተቀዳሚው ይኼ እናንተ የያዛችሁት መስመር ነውና! ማንኛውም መልካም ነገር ይሳካ ዘንድ ጊዜ ይወስዳል፤ ስለዚህ ከስኬት መድረሣችሁ አይቀርም! ፈጣሪ ይርዳችሁ!!!

    Like

  2. ውድ አዘጋጆች፣
    “አንድምታ” ወቅታዊ ብቻ ሳይሆን እሴቶቻችንን ማደራጃና ማሰባሰቢያ፣ ያማረበት መድረክ ነው።
    በርቱ። መጀመር ቀላል ስለሆነ፣ ጽናቱን ይስጣችሁ።

    Like

  3. ጥበብን ማሳደግ የሚቻለው ነባሩን በመከባከብና ስርጭቱን በማስፋት በመሆኑ አንድምታ መጽሔ ት የተንሳችበ ትጋት እጅግ የሚ ፈለግና የሚደነቅ ስለሆነ በርቱ።

    Like

  4. I am proud of your work. At a time when the majority of us are concerned about our daily lives – you have chosen to preserve and share the part of our culture that had once nourished our soul. Kum neger !

    Like

  5. አንድምታዎች በርቱ በመልካም ሥራችሁ ቀጥሉ፡ በጣም ሚገርም ሥራዎች ነው ምታቀርቡት በተለይ ሰሞኑን ስለ አንጋፋ የሙዚቃ ሰዎች የስብሃትና የሙሉቀን ቃለ መጠይቅ እጅግ ውብ ነበር፡ እዚህ አውስትራሊያ ትንሽ እንዳቅሚቲ የሥነ ጽሁፍ መተንፈሻ መድረክ በወር ምንገናኝባት አለች እና እዚያ ላይ አንድ ሁለት ሥራዎቻችሁን እነሆ ብያቸው እጅግ ተደመው ነበር፡ የበረቱ በቅርቡ ያገኟችኋል። ስለዚህ በርቱ ለማለት ነው ዛሬ ብቅ ያልኩት፡ ስለ ዳኛቸው ወርቁ ሥራዎች ካላቹ ብታካፍሉን እመኛለሁ፡ ከጣማችሁ ጥንጥ ስራዎችም ለለግስ ፈቃደኛ ነኝ።

    Like

  6. ኢንተርኔት ስጠቀም ቢኖረን ብዬ የምመኛቸው ላነባቸው የምፈልጋቸው ሁሉም አይነት ነገሮች በናንተ ዌብ ሳይት ላይ ተሰድረው በማግኘቴ ደስታዬ ወሰን የለውም። እናንት ትጉሀን የሀገሬ ሰዎች፤ ሁሉ ፖለቲከኛና የፖለቲካ ተንታኝ በሆነበት የሀገራችን የኢንተርኔት ሜዳ ጥቂት መናፈሻ፣ በበረሀ የተገኘ ንፁህ ኩልል ያለ ጥም ቆራጭ ውሀ ሆናችሁናል። እናመሰግናችሁዋለን! በርቱልን!

    Like

አስተያየት ለመስጠት

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s