“ጅብ ነች” (ልብወለድ)

“ልጄ እንግዲህ ትሰማ እንደሆነ የወለድኩህ እኔ ነኝ አንተ አይደለህም ስማኝ! ጅብ ትሆናለች ስልህ ጅብ ትሆናለች ነው። ይህን የአንተን አትሆንም የሚለውን መጽሐፍ ለዚያው ላዲስ አበባህ አድርገው!”

Read More

“ጉባኤው” (ልብወለድ)

መሪጌታ ስነ ኢየሱስ ብድግ ብለው ጃንሆይን ሽቅብ እየተመለከቱ፣ “ወንድሜ ነጋድራስ የተከበረውን ቋንቋችንን ሲዘነጣጥለው ባይ እንባዬ መጣ! … በመዠመሪያ ጅረት ማለት ሲገባው አናሳ ወንዝ አለን። ዝም አልነው። ቀጥዬ ማለት ሲገባው ለጥቄ ብሎ ተናገረ … እንግዲህ ይህን ዝም ብሎ ማለፍ እንደምን ይቻላል?”

Read More

“በሰንበት የተፀነሰው” (ልብወለድ)

አንድ ቀን ደግሞ ከገበያ ስትመለስ ዶሮ አባርሮ እንቁላሎቿን ሲሰባብር ደረሰችበት፡- “እንዴ? ምን እየሆንክ ነው?” አለችው። “እንቁላል ውስጥ ያሉትን ጫጩቶች እያስወጣሁዋቸው … እንቁላል ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ታፍነው ይሞታሉ ብዬ እኮ ነው! … እናት ልጆቿን ታስጨንቃለች? አታስጨንቅም አይደል?!”

Read More

የልብ ወለድ ሥነ ጽሑፍ ጉዞ

“በባህላችን የሒስ ጥበብ አልነበረም” የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ደራስያኑ መጻሕፍታቸው በጋዜጣም ሆነ በመጽሔት ሲተቹ አንዳንዶቹ ያኮርፋሉ፤ አንዳንዶቹ ይዝታሉ፤ አንዳንዶቹ በጋዜጣም ሆነ በመጽሔት ይሳደባሉ። ይኽ መንፈስ ከየት እንደመጣ አላውቅም።

Read More

አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’

ትረካው ውስጥ ወዳለው የዝምታ አወቃቀር ለመግባት ግን የሆነ ቀዳዳ ያስፈልገኛል። ዝምታን ተርትሬ ለመረዳት የሆነች ቁጢት ቆንጥጨ መያዝ ነበረብኝ። ይህቺ ቁጢት ‘ታስፈሩኛላችሁ’ የምትለዋ ቃል ናት።

Read More

አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’ (ክፍል 2)

ጃርሶ አትኳሪ ጸሐፊ ነው። ደስ የሚል ገላጭም ነው። ግን አስኮን ከንግግር ያወጣው ምክንያት ቢኖር ነው አልኩ። ገጾቹን በመጨመር ስለ አስኮ በተዘረዘረ መልክ ሊነግረን ይችል አልነበር? ለምን አላደረገውም?

Read More

አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’ (ክፍል 3)

በዚህ የአስኮ ጉዞ የምናየው ቀስ በቀስ ቋንቋ እየተሰወረ መሄዱንና አስኮ ያለበት ኢ-ሰብአዊ ሁኔታ መክረር ነው። ይሄ የቋንቋ መጥፋት ከሕብረተሰቡ በፍጹም ለመለያየት ፍጥጥሞሽ ማድረጉ ነው። አማራጭ አልነበረውም?

Read More

“አስኮ ጌታሁን” (ልብወለድ)

“እግዜር የሰውን ልጅ ሲፈጥር፣ ለጭቃ ማቡኪያ ሰባት ባልዲ ውሃ ያቀበልኩት እኔ ነኝ። ከፈለጋችሁ ሰማይ ቤት ስትገቡ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጠይቁ። እማኜ ናቸው”

Read More