ስለመጽሔቷ

“አንድምታ”

 

ከአስር ዓመታት በፊት በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ክበብ ስም “አንድምታ” የተሰኘች አንዲት የሥነጽሑፍ ልሳን እናዘጋጅ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ አንድምታ አድጋ በሰፊው “ጥበብ” ላይ የምታተኩር መጽሔት ሆና ቀርባለች። በዚችም መጽሔት የሥነ ጽሑፍ፣ ኪነ ጥበብ፣ ሥነ ሕንጻ፣ ኪነ ባህል እና ተመሳሳይ የጥበብ ዘርፎችን ለማቅረብ ፍላጎታችን ነው፡፡

አንድም፣ ጥበባዊ እይታ ብዙ አይነት መልክ የሚይዝ ነውና፤ አንድም ደግሞ፣ ጥበብን ለመረዳት ዘርፈ ብዙ ጥናት ይጠይቃልና። 

እስከዛሬ፣ በምንወዳቸውና በማንጠግባቸው ሥራዎች ስንመሰጥ፣ “መቼ ይሆን የሀገራችን ድርሰቶች የሚገባቸውን ክብር የሚያገኙት?” እያልን መብከንከናችን አልቀረም። ይህም የሚቻለው አንባቢዎች ከበርካታ ሺዎች ወደ ጥቂት ሚልዮኖች መድረስ ሲችሉ ይመስለናል።

እናም (በአቅማችን) የአንባቢውን ቁጥር ለመጨመር ጥበብን በ“አንድምታ” ለማቅረብ ወሰንን።

ኅሩይ አብዱ

ሕይወት ከተማ

ብሩክ አብዱ

7 thoughts on “ስለመጽሔቷ

 1. ሠናይ ሐሳብ ነው በርቱ! ትውልድ ከሚቀረጽበትና ከሚታነጽባቸው መንገዶች አንዱና ተቀዳሚው ይኼ እናንተ የያዛችሁት መስመር ነውና! ማንኛውም መልካም ነገር ይሳካ ዘንድ ጊዜ ይወስዳል፤ ስለዚህ ከስኬት መድረሣችሁ አይቀርም! ፈጣሪ ይርዳችሁ!!!

  Like

 2. ውድ አዘጋጆች፣
  “አንድምታ” ወቅታዊ ብቻ ሳይሆን እሴቶቻችንን ማደራጃና ማሰባሰቢያ፣ ያማረበት መድረክ ነው።
  በርቱ። መጀመር ቀላል ስለሆነ፣ ጽናቱን ይስጣችሁ።

  Like

 3. ጥበብን ማሳደግ የሚቻለው ነባሩን በመከባከብና ስርጭቱን በማስፋት በመሆኑ አንድምታ መጽሔ ት የተንሳችበ ትጋት እጅግ የሚ ፈለግና የሚደነቅ ስለሆነ በርቱ።

  Like

አስተያየት ለመስጠት

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s