“የጉለሌው ሰካራም” (ልብወለድ)
“እንግዲህ መንገደኛው ሁሉ ‘ይህ የማን ቤት ነው?’ ብሎ ሲጠይቅ የተበጀ ሊባል ነው … ‘ተበጀ የትኛው ነው?’ ሲባል ‘ዶሮ ነጋዴው’ ሊባል ነው … ‘ዶሮ ነጋዴው የትኛው ነው?’ ሲባል ‘ያ የጉለሌው ሰካራም’ ሊባል ነው … አወይ! እኔ ተበጀ … ተበላሽቻለሁ!” Continue reading “የጉለሌው ሰካራም” (ልብወለድ)
“እንግዲህ መንገደኛው ሁሉ ‘ይህ የማን ቤት ነው?’ ብሎ ሲጠይቅ የተበጀ ሊባል ነው … ‘ተበጀ የትኛው ነው?’ ሲባል ‘ዶሮ ነጋዴው’ ሊባል ነው … ‘ዶሮ ነጋዴው የትኛው ነው?’ ሲባል ‘ያ የጉለሌው ሰካራም’ ሊባል ነው … አወይ! እኔ ተበጀ … ተበላሽቻለሁ!” Continue reading “የጉለሌው ሰካራም” (ልብወለድ)
“አለቃ ዘነብ የተማሩ ሊቅ ነበሩ … እርሳቸውም በውስጡ እጅግ የረቀቀ ምስጢር ያለበት መጽሐፈ ጨዋታ የሚባል መጽሐፍ ትተው ስለሞቱ ስማቸው አልጠፋም።” Continue reading አለቃ ዘነብ (፲፰፻፲፯-፲፰፻፷፱)
ባባቱ የሚኮራ ሰው ጅል ነው። የሰው አባቱ አንድ አዳም አይደለምን? ሴትን ወንድ አንድ ጊዜ ይደርስባታል መንታ ትወልዳለች። እህልም አንዲት ፍሬ ተዘርታ ብዙ ታፈራለች። ይህ ነገር ከቶ እንዴት ነው? እንጃ ማን ያውቀዋል። Continue reading “መጽሐፈ ጨዋታ” (ቅንጫቢ)
አዝማሪ ጣፋጭ በቋረኛው ካሳ ጦር ተማርኳል። ጣፋጭ፣ የደጃች ጎሹ አዝማሪ ስለነበር በብዙ ጦር ሜዳ ላይ ውሏል። ተስፋና ፍርሀት ከፊቱ ተደቅነዋል። ባንድ በኩል፣ አዝማሪን መግደል ነውር የሚያደርገው ባህል ጋሻ ሁኖት ከክፉ እንደሚታደገው ተስፋ ያደርጋል። በሌላ በኩል፣ ደጃዝማች ካሳ ይህን ደምብ ለማክበራቸው እርግጠኛ አይደለም። Continue reading መሰንቆ እና ብትር (ወግ)
ባላ የምሽተታ ኦያት በሰማ ቍጥር ኽይን ይጠውጥን። በኸረም ጭን የምስም ኸማ ኤኽይርፕወ ኸማ እንጐድ ጮዳ ይትጮድ። ኧከሰም ኧከሰም በሜየቴ የትገተረች እርስየ ገረደታ ደንጋኽይታ በፍወረጀታ ይሟሽና … Continue reading “የሺንጋ ቃያ” (ልብወለድ)
ባላ የሚስቱን የስቃይ ድምጽ በሰማ ቁጥር ጭንቀት ላይ ይወድቃል። ሆኖም ወንድ ነውና ጭንቀቱ እንዳይታወቅበት አፍኖ ይዞ ሌላ ጨዋታ ያመጣል። አልፎ አልፎም በአጠገቡ የተኛችውን ትንሿ ልጁን ባይበሉባው ጉንጯን ይዳስሳታል … Continue reading “የሺንጋ መንደር” (ልብወለድ)
‘አሞራና ቅል ተጋቡ። ቅሉ ተሰበረ። አሞራውም በረረ።’ … አጭር ልብወለድ ታሪክ ልክ እንደዚህ እጥር፣ ምጥን፣ ጣፈጥ ማለት አለበት። Continue reading የአጭር ልብወለድ ታሪክ
“ልጄ እንግዲህ ትሰማ እንደሆነ የወለድኩህ እኔ ነኝ አንተ አይደለህም ስማኝ! ጅብ ትሆናለች ስልህ ጅብ ትሆናለች ነው። ይህን የአንተን አትሆንም የሚለውን መጽሐፍ ለዚያው ላዲስ አበባህ አድርገው!” Continue reading “ጅብ ነች” (ልብወለድ)
ቀሚሱን እስከ እግር ጣቱ ሰዶ ወንዱንም ሴቱንም በቶኪዩ ጐዳና ድምቡል ድምቡል ሲል ያሳዩሃል። እንዲህ አስተዋውቀውህ ከቤቱ ሲወስዱህ ተንበርክኮ ይቆይሃል፤ “ንበር ሊለኝ ነው ሊነሳልኝ ነው” ስትል ፍግም ብሎ መሬት ይስምልሃል። አደግድግ አንተም … እንዳገርህ ‘ክበር ተከባበር’ ነውና እጅ ንሳ። Continue reading ማኅደረ ብርሃን – ሀገረ ጃፓን
የካቲት 3 ቀን በጃፓን የክረምት ማጋመሻ በዓል ይባላል። በዚህም በዓል ቤተ ዘመዱ ሁሉ በየቤቱ እየተሰበሰበ ቆሎ እየተቆላ ‘ሰይጣንና ክፉ ነገር ውጣ … ሲሳይና ጤና ወደ ቤት ግባ’ እያለ ቆሎውን እየዘገነ ይበትናል፤ የተረፈውንም ይበሉታል። ይኸውም ባገራችን በኢትዮጵያ በየባላገሩ ለእንቁጣጣሽና ለግንቦት ልደታ እንደሚደረገው ነው። Continue reading የጃፓን ባህል ቅኝት