አፈወርቅ ተክሌ እና “ቪላ አልፋ”
እንዲህ የመሰለውን መኖሪያ ቤት ለመሥራት ምን እንዳሳሰበው እንዲነግረኝ አፈወርቅን ጠይቄው ነበር። ለማናገር ፈቃደኛ ቢሆንም … አናጢዎቹ በየደቂቃው ይጠሩታል … ገና ተመልሶ ቁጭ ከማለቱም ቀለም ቀቢዎች ይጠሩታል። Continue reading አፈወርቅ ተክሌ እና “ቪላ አልፋ”
እንዲህ የመሰለውን መኖሪያ ቤት ለመሥራት ምን እንዳሳሰበው እንዲነግረኝ አፈወርቅን ጠይቄው ነበር። ለማናገር ፈቃደኛ ቢሆንም … አናጢዎቹ በየደቂቃው ይጠሩታል … ገና ተመልሶ ቁጭ ከማለቱም ቀለም ቀቢዎች ይጠሩታል። Continue reading አፈወርቅ ተክሌ እና “ቪላ አልፋ”
“መጀመሪያ በአምስት ብር ነበር የሚሸጠው። ነገር ግን አልሄድ ስላለ አስር ብር አደረግሁት። አሁንም እንደገና አልሄድ አለ። ስለዚህ መሸጫ ዋጋውን አስራ አምስት ብር አድርጌዋለሁ” አለኝ። ይህንን ስሰማ ሳቅ ወጥሮ ያዘኝ። ነገር ግን ዳኛቸውን እንዳላስቀይመው በመፍራት ሳቄን ታግዬ አስቀረሁት። Continue reading ዳኛቸው ወርቁና መጽሐፎቹ
የስናፍቅሽ የአሳሳል ጥንካሬ በ“ቅርጻዊ” ስልት ሸራዋን ማድመቅ እንደሆነ ግልጽ ነው። መስመሮቿን በሚገባ ትስላለች። ቀለሞቿን ደግሞ አነባብራ ትጠቀማለች። ሰፋ ያለ ምሕዋር መፍጠርንም የግሏ አድርጋዋለች። Continue reading “በራሪ ወፎች” (የሥዕል እይታ)
ይሁን እንጅ ኢትዮጵያዊ የሆነ አሳብ፣ ኢትዮጵያዊ በሆነ ንግግር የመግለጹ ዕድል ለግዕዝ ቀርቶበት ለአማርኛ ሆኗል። አማርኛው ዛሬ ዘመን የማንናገርበትና የማንጽፈው፣ ለማስተዋሉም የሚያስቸግረንና የሰዋስው አካሔዱ የተለዋወጠ ብዙ ቃልና አገባብ አለበት። Continue reading ስለ ኢትዮጵያ ደራስያን
የኢትዮጵያን የጥንቱን ትምህርት ከሚያውቁት ሊቃውንት አማርኛንና ግዕዝን ለማጣራት፣ ያለቃ ኪዳነ ወልድን ያህል የሚደክም ብዙ አልተገኘም። Continue reading የግዕዝ ሊቃውንት እና አዲሱ ዘመን
አማርኛ ማሠሪያ አንቀጹን አርቆ፤ ከማህሉ ልዩ ልዩ አሳብ ጣልቃ ማግባት የተፈጥሮ ጠባዩ ነው ብለናል። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ይህን ሳይከተሉ ንግግሩን ባጭር ባጭሩ ማሠር ልዩ ባሕርያቸው ነው። አንዳንድ ሰው ብላቴን ጌታ ኅሩይ አማርኛን በውጭ አገር ንግግር እንጂ በተፈጥሮ ጠባዩ አያስኬዱትም ብሎ ጽፎባቸዋል። Continue reading ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ
ኬዎርኮፍ ከአጎቱ ጋር በመሆን ከጅቡቲ ትንባሆ ወደ ፈረሳይ ሐገር በመላክ ትልቅ ንግድ ጀመሩ። ቀስ እያለም ንግዱን ወደ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ እና አዲስ አበባ አስፋፋ። ጎራዴ፣ ሰይፍ፣ ጩቤ እና የመሳሰሉትን በ1890ዎቹ በሐረር ያመርት እንደነበር አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። Continue reading ማቲክ ኬዎርኮፍ – አርመኑ ነጋዴ
በጅሮንድ ተክለሐዋርያት ፍጹም አማርኛ በሆነ ግጥም ጥቂት ተረት ጽፈው ካሳተሙና በተረት ዓይነት ቲያትር ከጻፉ በኋላ፣ አሁንም ንጹሕ በሆነ አማርኛ ስለ እርሻ ትምህርት ጽፈዋል። Continue reading የ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ደራሲዎች
በሚያዝያ 1928 መጨረሻ ላይ የአዲስ አበባ ሕዝብ አራዳን መዝረፍ እና ማውደም ጀመረ። የኬዎርኮፍ ሱቅም ይህ እጣ አልቀረለትምና ከአካባቢው ሕንጻዎች ጋር ተቃጥሎ በአጥንቱ ቀረ። በአሁኑ ጊዜ ይህ ህንጻ ሮያል ኮሌጅን፣ አቢሲኒያ ባንክን እና ካስቴሊ ሬስቶራንትን በውስጡ ያስተናግዳል። Continue reading የፒያሳው ኬዎርኮፍ ሕንጻ
ወደ ሥነጽሑፍ ከመግባቴ በፊት ሥዕል እሞክር ነበር። ሥዕሎቹ ለግጥሞቹ ወይም ለታሪኩ እንደ ማስረጃ ወይንም ምትክ እንዲሆኑ ብዬ አይደለም። በራሳቸው መንገድ እንደ ቅኔ እንደ ሀሳብ እንዲታዩ ነው። Continue reading “በዕውቀቱ ሥዩም” (ቃለመጠይቅ)