“አሞራ … የዳዊት አሞራ” (ግጥም)
“አሞራ የዳዊት አሞራ
ተከተለኝ በኋላ፤
ሥጋ ላብላህ ከበላ
ደም ላጠጣህ መራራ
ተከተለኝ በኋላ …” Continue reading “አሞራ … የዳዊት አሞራ” (ግጥም)
“አሞራ የዳዊት አሞራ
ተከተለኝ በኋላ፤
ሥጋ ላብላህ ከበላ
ደም ላጠጣህ መራራ
ተከተለኝ በኋላ …” Continue reading “አሞራ … የዳዊት አሞራ” (ግጥም)
ሰፈሬ አምባሳደር ሲኒማ ቤትም እገባ የነበረው፣ ከስድስት እስከ ዐሥራ ኹለት ሰዐት፥ ሦስት ፊልም በሦስት ብር በነበረበት ጊዜ ነበር። ያኔ ያየኋቸው ፊልሞች የሥነ ጽሑፍ ፍቅር ሰጥተውኛል። Continue reading “መሐመድ ኢድሪስ” (ቃለመጠይቅ)
“እያልከኝ ያለኸው፣ ሞትን አየው ነው?” አልሁና ሣቅ አልሁኝ … እሱ ግን አልሣቀም። ድርቅና ፍጥጥ ብሎ ተመለከተኝ። ወዲያው፣ ፈገግታዬ ጠፍቶ፥ በውስጤ ፍርሃት ነገሠ። Continue reading “የእኩለ ሌሊት ወግ” (ልብወለድ)
አንድ ሰሞን የአንድ ሥራ-ሀላፊን ቃለመጠይቅ አንብቤ ሃያ ሦስት የእንግሊዝኛ ቃላት/ሐረጎች ተቀላቅለውበት አገኘሁ! ታዲያ “ይቺ ምን አላትና ሰው ታስተቻለች?” ያሰኝ ይሆናል። Continue reading “ሳይቸግር ጤፍ ብድር” (ወግ)
አምስተኛ ክፍል ነበር። I am Legend የተባለውን መጽሐፍ አንዲት ጓደኛዬን “እንተርጉመው” ብያት በጠራራ ፀሐይ ይዘነው ሜዳ ላይ ቁጭ ብለን ሞከርን። አንድ አረፍተ ነገር እንኳን አልተሳካልንም። Continue reading “ሕይወት ታደሰ” (ቃለመጠይቅ)
“ተመቅጽበት የታላቅ ክብር ራእይ በፊቴ ውልብ አለብኝ። የተማረና ትልቅ ሰው ኾኜ እሚያሳይ ምስል ዐይኔ ላይ አለፈ። የምንደራችንም ሰዎች ተመኻከላቸው የወጣውን ሊቅ በታላቅ አክብሮት ለመቀበል ወደ ቤታችን ጎረፉ። ሴቶች ዕልልታቸውን አቀለጡት።” Continue reading “ኀሠሣ” (ልብወለድ)
ልጅነቴ በትረካ የተሞላ ነበር። አያቴ ከተረከችልኝ ውስጥ “የዋህ ባልና ሚስቶቹ” እንዲሁም “የአያ ድቡልቡሌን” ታሪክ ሳስታውስ አሁን ራሱ ምናቤ በግልፅ በተሳለ ጣፋጭ ትውስታ ይሞላል። Continue reading “ሙሉጌታ አለባቸው” (ቃለመጠይቅ)
እማማ አስረበብ የራሳቸውን ስኒ ይዘው ባይመጡም ረከቦት ላይ ከሚደረደሩ ስኒዎች መካከል መርጠው ለራሳቸው የሰየሟት ሸራፋ ስኒ ነበረቻቸው። ሰርኬ ተሳስታ በሌላ ስኒ የሰጠቻቸው እንደሆነ “በራሴ ፍንጃል ካልሆነ ባልጠጣ ይሻለኛል” ብለው ይመልሳሉ። Continue reading “ማሪበላ” (ልብወለድ)
… አንድ ጊዜ ተአድዋ ዘመቻ በዋላ ትልቅ ግብር ያዘጋጃሉ … በመጨረሻ ዕለት ንግሥት ጠጋ አሉኝና ‘ለመሆኑ ያንን ዱባሽን በትልቁ ለብዙ ሰው መስራት ትችያለሽ?’ ይሉኛል። ተጠራጠርኩ። ‘እንዴ አንቺ ጎራዳ እናደርገውና እምቢ ካለን ዝም ነው’ አሉ … ሂሂሂሂ … Continue reading “ፍቅር እና ሆሄ” (ልብወለድ)
ብዙ ትውልድ አልፎ ለትውልድ ደርሼ፣
ደግሞ በዚያው መንገድ መጣሁ ተመልሼ።
Continue reading “ዓለም እና ጊዜ” (ግጥም)