የበአሉ ግርማ ገጸባሕርያት

በአሉ ግርማ በ“ከአድማስ ባሻገር” ገጸባሕርያቱን ሲስል እጅጉን ተጠብቦበት እንደነበር ያስታውቃል። የመጀመሪያው ልብወለዱ መሆኑን ስናስታውስ ደግሞ የበለጠ ግሩም ባለሙያነቱን ያሳየናል። Continue reading የበአሉ ግርማ ገጸባሕርያት

“ከአድማስ ባሻገር” (ልብወለድ)

“ማን ነኝ? ምንስ ነኝ? እቃ። ለዚያውም ዋጋ የሌለው የበሰበሰ እቃ። እቃ ሆኜ እንድቀር ያደረገኝ ማንነው? እኔው ራሴ? ወይስ ያፈራኝ ህብረተሰብ? ወይስ አልፌው የመጣሁት የትምህርት አቋም? … እኔ ግን ማንነኝ?” Continue reading “ከአድማስ ባሻገር” (ልብወለድ)

የደራስያኑ ጦርነት

ከመሠረቱ በሥነጥበብ አካባቢ የአስተያየት ግጭት አዲስ ነገር አይደለም። የመናናቅና የመቀናናት ስሜት አለ። የሥነጥበብ ሰዎችም፣ እንደሌላው ሁሉ ደካማ ፍጡሮች ናቸውና … የሥነጽሑፍ ጦርነትም አራጋቢዎችና አስታራቂዎች፣ ዝምተኛ ተመልካቾች፣ ሦስተኛ ኀይል ለመሆን የሚፈልጉ ገለልተኞች አሉበት። Continue reading የደራስያኑ ጦርነት

ውሎ ከጋሽ ጸጋዬ ጋር

“ ‘ሕይወት ቢራቢሮ’ የተሰኘችው ግጥሜ በጋዜጣ ታትማ በወጣች ማግስት መንግሥቱ ለማ ከቢሮዬ መጥቶ፣ ‘ቢራውን እስቲ አምጣው ወይስ ዝም ብለህ ነው ቢራ ቢሮ ያልከው!’ ብሎ እንደቀለደብኝ ትዝ ይለኛል … አሁን እኮ ደማም ቋንቋ የሚናገር ሰው ሁሉ ጠፋ” ብለው ጋሽ ጸጋዬ ትክዝ አሉ። Continue reading ውሎ ከጋሽ ጸጋዬ ጋር

“የጉለሌው ሰካራም” (ልብወለድ)

“እንግዲህ መንገደኛው ሁሉ ‘ይህ የማን ቤት ነው?’ ብሎ ሲጠይቅ የተበጀ ሊባል ነው … ‘ተበጀ የትኛው ነው?’ ሲባል ‘ዶሮ ነጋዴው’ ሊባል ነው … ‘ዶሮ ነጋዴው የትኛው ነው?’ ሲባል ‘ያ የጉለሌው ሰካራም’ ሊባል ነው … አወይ! እኔ ተበጀ … ተበላሽቻለሁ!” Continue reading “የጉለሌው ሰካራም” (ልብወለድ)

“መጽሐፈ ጨዋታ” (ቅንጫቢ)

ባባቱ የሚኮራ ሰው ጅል ነው። የሰው አባቱ አንድ አዳም አይደለምን? ሴትን ወንድ አንድ ጊዜ ይደርስባታል መንታ ትወልዳለች። እህልም አንዲት ፍሬ ተዘርታ ብዙ ታፈራለች። ይህ ነገር ከቶ እንዴት ነው? እንጃ ማን ያውቀዋል። Continue reading “መጽሐፈ ጨዋታ” (ቅንጫቢ)

“የሺንጋ ቃያ” (ልብወለድ)

ባላ የምሽተታ ኦያት በሰማ ቍጥር ኽይን ይጠውጥን። በኸረም ጭን የምስም ኸማ ኤኽይርፕወ ኸማ እንጐድ ጮዳ ይትጮድ። ኧከሰም ኧከሰም በሜየቴ የትገተረች እርስየ ገረደታ ደንጋኽይታ በፍወረጀታ ይሟሽና … Continue reading “የሺንጋ ቃያ” (ልብወለድ)

“የሺንጋ መንደር” (ልብወለድ)

ባላ የሚስቱን የስቃይ ድምጽ በሰማ ቁጥር ጭንቀት ላይ ይወድቃል። ሆኖም ወንድ ነውና ጭንቀቱ እንዳይታወቅበት አፍኖ ይዞ ሌላ ጨዋታ ያመጣል። አልፎ አልፎም በአጠገቡ የተኛችውን ትንሿ ልጁን ባይበሉባው ጉንጯን ይዳስሳታል … Continue reading “የሺንጋ መንደር” (ልብወለድ)