ማኅደረ ብርሃን – ሀገረ ጃፓን

ቀሚሱን እስከ እግር ጣቱ ሰዶ ወንዱንም ሴቱንም በቶኪዩ ጐዳና ድምቡል ድምቡል ሲል ያሳዩሃል። እንዲህ አስተዋውቀውህ ከቤቱ ሲወስዱህ ተንበርክኮ ይቆይሃል፤ “ንበር ሊለኝ ነው ሊነሳልኝ ነው” ስትል ፍግም ብሎ መሬት ይስምልሃል። አደግድግ አንተም … እንዳገርህ ‘ክበር ተከባበር’ ነውና እጅ ንሳ። Continue reading ማኅደረ ብርሃን – ሀገረ ጃፓን

የጃፓን ባህል ቅኝት

የካቲት 3 ቀን በጃፓን የክረምት ማጋመሻ በዓል ይባላል። በዚህም በዓል ቤተ ዘመዱ ሁሉ በየቤቱ እየተሰበሰበ ቆሎ እየተቆላ ‘ሰይጣንና ክፉ ነገር ውጣ … ሲሳይና ጤና ወደ ቤት ግባ’ እያለ ቆሎውን እየዘገነ ይበትናል፤ የተረፈውንም ይበሉታል። ይኸውም ባገራችን በኢትዮጵያ በየባላገሩ ለእንቁጣጣሽና ለግንቦት ልደታ እንደሚደረገው ነው። Continue reading የጃፓን ባህል ቅኝት

ግስ ዘመምህር ክፍሌ

አለቃ ኪዳነ ወልድ እንደሚሉት መምህር ክፍለ ጊዮርጊስን ለመዝገበ ቃላት ሥራ ያነሳሳቸው የዲልማን መጽሐፍ ነው። ሆኖም የመምህር ክፍሌ ግስ በቃላት አመራረጥና አፈታት እንዲሁም በጥቅስ ምርጫው የራሱን መንገድ የቀየሰ ይመስላል። Continue reading ግስ ዘመምህር ክፍሌ

“ጉባኤው” (ልብወለድ)

መሪጌታ ስነ ኢየሱስ ብድግ ብለው ጃንሆይን ሽቅብ እየተመለከቱ፣ “ወንድሜ ነጋድራስ የተከበረውን ቋንቋችንን ሲዘነጣጥለው ባይ እንባዬ መጣ! … በመዠመሪያ ጅረት ማለት ሲገባው አናሳ ወንዝ አለን። ዝም አልነው። ቀጥዬ ማለት ሲገባው ለጥቄ ብሎ ተናገረ … እንግዲህ ይህን ዝም ብሎ ማለፍ እንደምን ይቻላል?” Continue reading “ጉባኤው” (ልብወለድ)

“እንዳለጌታ ከበደ” (ቃለመጠይቅ)

ለመጀመሪያ ጊዜ ግጥም የጻፍኩት ሰባተኛ ክፍል እያለሁ ነው። ይህን ያህል ከባድ አይደለም ብዬ አንድ ግጥም ጽፌ ለመምህሩ ሰጠሁ። መምህሩ ግን ከድርሰቱ ይልቅ የወደደው እጅ ጽሑፌን ነበር። Continue reading “እንዳለጌታ ከበደ” (ቃለመጠይቅ)

“በሰንበት የተፀነሰው” (ልብወለድ)

አንድ ቀን ደግሞ ከገበያ ስትመለስ ዶሮ አባርሮ እንቁላሎቿን ሲሰባብር ደረሰችበት፡- “እንዴ? ምን እየሆንክ ነው?” አለችው። “እንቁላል ውስጥ ያሉትን ጫጩቶች እያስወጣሁዋቸው … እንቁላል ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ታፍነው ይሞታሉ ብዬ እኮ ነው! … እናት ልጆቿን ታስጨንቃለች? አታስጨንቅም አይደል?!” Continue reading “በሰንበት የተፀነሰው” (ልብወለድ)

የልብ ወለድ ሥነ ጽሑፍ ጉዞ

“በባህላችን የሒስ ጥበብ አልነበረም” የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ደራስያኑ መጻሕፍታቸው በጋዜጣም ሆነ በመጽሔት ሲተቹ አንዳንዶቹ ያኮርፋሉ፤ አንዳንዶቹ ይዝታሉ፤ አንዳንዶቹ በጋዜጣም ሆነ በመጽሔት ይሳደባሉ። ይኽ መንፈስ ከየት እንደመጣ አላውቅም። Continue reading የልብ ወለድ ሥነ ጽሑፍ ጉዞ

አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’

ትረካው ውስጥ ወዳለው የዝምታ አወቃቀር ለመግባት ግን የሆነ ቀዳዳ ያስፈልገኛል። ዝምታን ተርትሬ ለመረዳት የሆነች ቁጢት ቆንጥጨ መያዝ ነበረብኝ። ይህቺ ቁጢት ‘ታስፈሩኛላችሁ’ የምትለዋ ቃል ናት። Continue reading አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’