አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’ (ክፍል 2)

ጃርሶ አትኳሪ ጸሐፊ ነው። ደስ የሚል ገላጭም ነው። ግን አስኮን ከንግግር ያወጣው ምክንያት ቢኖር ነው አልኩ። ገጾቹን በመጨመር ስለ አስኮ በተዘረዘረ መልክ ሊነግረን ይችል አልነበር? ለምን አላደረገውም? Continue reading አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’ (ክፍል 2)

አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’ (ክፍል 3)

በዚህ የአስኮ ጉዞ የምናየው ቀስ በቀስ ቋንቋ እየተሰወረ መሄዱንና አስኮ ያለበት ኢ-ሰብአዊ ሁኔታ መክረር ነው። ይሄ የቋንቋ መጥፋት ከሕብረተሰቡ በፍጹም ለመለያየት ፍጥጥሞሽ ማድረጉ ነው። አማራጭ አልነበረውም? Continue reading አስኮ ጌታሁን እና ‘ዝምታ’ (ክፍል 3)

ዳኛቸው ወርቁና መጽሐፎቹ

“መጀመሪያ በአምስት ብር ነበር የሚሸጠው። ነገር ግን አልሄድ ስላለ አስር ብር አደረግሁት። አሁንም እንደገና አልሄድ አለ። ስለዚህ መሸጫ ዋጋውን አስራ አምስት ብር አድርጌዋለሁ” አለኝ። ይህንን ስሰማ ሳቅ ወጥሮ ያዘኝ። ነገር ግን ዳኛቸውን እንዳላስቀይመው በመፍራት ሳቄን ታግዬ አስቀረሁት። Continue reading ዳኛቸው ወርቁና መጽሐፎቹ

ስለ ኢትዮጵያ ደራስያን

ይሁን እንጅ ኢትዮጵያዊ የሆነ አሳብ፣ ኢትዮጵያዊ በሆነ ንግግር የመግለጹ ዕድል ለግዕዝ ቀርቶበት ለአማርኛ ሆኗል። አማርኛው ዛሬ ዘመን የማንናገርበትና የማንጽፈው፣ ለማስተዋሉም የሚያስቸግረንና የሰዋስው አካሔዱ የተለዋወጠ ብዙ ቃልና አገባብ አለበት። Continue reading ስለ ኢትዮጵያ ደራስያን

ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ

አማርኛ ማሠሪያ አንቀጹን አርቆ፤ ከማህሉ ልዩ ልዩ አሳብ ጣልቃ ማግባት የተፈጥሮ ጠባዩ ነው ብለናል። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ይህን ሳይከተሉ ንግግሩን ባጭር ባጭሩ ማሠር ልዩ ባሕርያቸው ነው። አንዳንድ ሰው ብላቴን ጌታ ኅሩይ አማርኛን በውጭ አገር ንግግር እንጂ በተፈጥሮ ጠባዩ አያስኬዱትም ብሎ ጽፎባቸዋል። Continue reading ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ

የ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ደራሲዎች

በጅሮንድ ተክለሐዋርያት ፍጹም አማርኛ በሆነ ግጥም ጥቂት ተረት ጽፈው ካሳተሙና በተረት ዓይነት ቲያትር ከጻፉ በኋላ፣ አሁንም ንጹሕ በሆነ አማርኛ ስለ እርሻ ትምህርት ጽፈዋል። Continue reading የ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ደራሲዎች

“በዕውቀቱ ሥዩም” (ቃለመጠይቅ)

ወደ ሥነጽሑፍ ከመግባቴ በፊት ሥዕል እሞክር ነበር። ሥዕሎቹ ለግጥሞቹ ወይም ለታሪኩ እንደ ማስረጃ ወይንም ምትክ እንዲሆኑ ብዬ አይደለም። በራሳቸው መንገድ እንደ ቅኔ እንደ ሀሳብ እንዲታዩ ነው። Continue reading “በዕውቀቱ ሥዩም” (ቃለመጠይቅ)

አለቃ ታየ እና የዘመኑ ደራሲዎች

አማርኛ በዚህ አኳኋን ሲጐላደፍ ቆይቶ ወደዚህ ዘመን ይደርሳል። ይሁን እንጂ በጭራሽ ነፃ ወጥቶ ግዕዝ ባልተቀላቀለበት ንጹሕ በሆነ አማርኛ የተጻፈው መጽሐፍ የአጤ ቴዎድሮስ ታሪክ ነው። Continue reading አለቃ ታየ እና የዘመኑ ደራሲዎች