-
“ወደ አዲስ አበባ” (ወግ)
“ሙሉ እንጀራ በሽሮ ወጥ በአስር ሳንቲም፣ በክንድ የሚለካ ፉርኖ በአስር ሳንቲም፣ አንድ ብርጭቆ ሻይ በአምስት ሳንቲም ይገዛ ነበር። የዚያም ዓይነት ዓለም ነበር … በሺ ዘጠኝ መቶ አርባዎቹ መጀመሪያ ላይ!”
-
“የፈላስፋው ውሃ” (ወግ)
“የሚዘንበው ዝናብ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ ሰውም ሆነ እንስሳም ሆነ ፍጡር የተባለን ሁሉ ይመርዛል። ውሀን የጠጣ ሁሉ ያብዳል። ተዚህ የበለጠ ምን የሚያሳዝንና የሚያስተክዘኝ አለ?”
-
“ያጼ ዳዊት ጀብዱ” (ክፍል 2)
“የኔም ሰው በነፍጥ ያልቃል። የርስዎም ሰው በሟርት ያልቃል። እኔም አልሞትም እርስዎም አይሞቱ … ምነው በፍቅር ብንለያይ አይሻልም?”
-
“ሌሊሳ ግርማ” (ቃለመጠይቅ)
የአጭር ልብ ወለድን ቅርፅ እወደዋለሁኝ … እና መፃፍ ፈልጌ ብዕር ስሰነዝር በቀላሉ ምናባዊ እና አጭር ፅሁፍ ይሆንብኛል። መሆኑንም አልጠላውም። እኔ ባነብ የምወደውን አይነት ፅሁፍ ብፅፍ ደስ ይለኛል እንጂ አይከፋኝም።
-
“ልብወለድ ታሪክ” (ጦቢያ)
“ሣር ልጭድ ቢል የለሰለሰው የጨዋ እጁ እንደሽንኵርት ተላጠ። ብርጭቆ ብርሌ በሚጨብጥበት በነበረው ጣቱ ምሳር ቢጨብጥበት ጉብር አወጣ። ያም ሆነ ያም ሆነ ያው የጥንት ደጃዝማች የዛሬው ባሪያ አዲሱ ጌታው እንዳይቈጣው ሥራውን አልሁህ አልሁህ ይል ጀመር።”