-
“ገብረ ክርስቶስ ገጣሚው”
ገብረ ክርስቶስ ጋር ሐረር ባዶ እግራችንን፣ በቴኒስ ኩዋስ ተጫውተናል። ገብረ ክርስቶስ፣ የእግር ጣቶቹ እኩል ስለሆኑ፣ ኳሱን የሚመታ በእግር ኩርኩም ነበር – ኹሌ የከረረች ምት።
-
“ዐፅም” (ግጥም)
ንጉሥ ኖረኻል ወይ፣ ኖረኻል ወይ ጌታ ወይ ቁሩንጮ ለባሽ፣ ለማኙ ከርታታ ሚኒስትር ደጃዝማች፣ ወይም ፊታውራሪ ባለብዙ ገንዘብ፣ አሽከር አሳዳሪ
-
“መሐመድ ኢድሪስ” (ቃለመጠይቅ)
ሰፈሬ አምባሳደር ሲኒማ ቤትም እገባ የነበረው፣ ከስድስት እስከ ዐሥራ ኹለት ሰዐት፥ ሦስት ፊልም በሦስት ብር በነበረበት ጊዜ ነበር። ያኔ ያየኋቸው ፊልሞች የሥነ ጽሑፍ ፍቅር ሰጥተውኛል።
-
“የእኩለ ሌሊት ወግ” (ልብወለድ)
“እያልከኝ ያለኸው፣ ሞትን አየው ነው?” አልሁና ሣቅ አልሁኝ … እሱ ግን አልሣቀም። ድርቅና ፍጥጥ ብሎ ተመለከተኝ። ወዲያው፣ ፈገግታዬ ጠፍቶ፥ በውስጤ ፍርሃት ነገሠ።
-
“ሳይቸግር ጤፍ ብድር” (ወግ)
አንድ ሰሞን የአንድ ሥራ-ሀላፊን ቃለመጠይቅ አንብቤ ሃያ ሦስት የእንግሊዝኛ ቃላት/ሐረጎች ተቀላቅለውበት አገኘሁ! ታዲያ “ይቺ ምን አላትና ሰው ታስተቻለች?” ያሰኝ ይሆናል።
-
“ሕይወት ታደሰ” (ቃለመጠይቅ)
አምስተኛ ክፍል ነበር። I am Legend የተባለውን መጽሐፍ አንዲት ጓደኛዬን “እንተርጉመው” ብያት በጠራራ ፀሐይ ይዘነው ሜዳ ላይ ቁጭ ብለን ሞከርን። አንድ አረፍተ ነገር እንኳን አልተሳካልንም።
-
“ኀሠሣ” (ልብወለድ)
“ተመቅጽበት የታላቅ ክብር ራእይ በፊቴ ውልብ አለብኝ። የተማረና ትልቅ ሰው ኾኜ እሚያሳይ ምስል ዐይኔ ላይ አለፈ። የምንደራችንም ሰዎች ተመኻከላቸው የወጣውን ሊቅ በታላቅ አክብሮት ለመቀበል ወደ ቤታችን ጎረፉ። ሴቶች ዕልልታቸውን አቀለጡት።”
-
“አበባየሆሽ” (ሥነ ቃል)
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን ጌቶች አሉ ብለን ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን እሜቴ አሉ ብለን እውዬ (እኸ) እዋውዬ ካሽከር ተዋውዬ ጌቶች አሉ ብዬ ገባሁ ሰተት ብዬ