-
“ሙሉጌታ አለባቸው” (ቃለመጠይቅ)
ልጅነቴ በትረካ የተሞላ ነበር። አያቴ ከተረከችልኝ ውስጥ “የዋህ ባልና ሚስቶቹ” እንዲሁም “የአያ ድቡልቡሌን” ታሪክ ሳስታውስ አሁን ራሱ ምናቤ በግልፅ በተሳለ ጣፋጭ ትውስታ ይሞላል።
-
“ማሪበላ” (ልብወለድ)
እማማ አስረበብ የራሳቸውን ስኒ ይዘው ባይመጡም ረከቦት ላይ ከሚደረደሩ ስኒዎች መካከል መርጠው ለራሳቸው የሰየሟት ሸራፋ ስኒ ነበረቻቸው። ሰርኬ ተሳስታ በሌላ ስኒ የሰጠቻቸው እንደሆነ “በራሴ ፍንጃል ካልሆነ ባልጠጣ ይሻለኛል” ብለው ይመልሳሉ።
-
“ፍቅር እና ሆሄ” (ልብወለድ)
… አንድ ጊዜ ተአድዋ ዘመቻ በዋላ ትልቅ ግብር ያዘጋጃሉ … በመጨረሻ ዕለት ንግሥት ጠጋ አሉኝና ‘ለመሆኑ ያንን ዱባሽን በትልቁ ለብዙ ሰው መስራት ትችያለሽ?’ ይሉኛል። ተጠራጠርኩ። ‘እንዴ አንቺ ጎራዳ እናደርገውና እምቢ ካለን ዝም ነው’ አሉ … ሂሂሂሂ …
-
የበአሉ ግርማ ገጸባሕርያት
በአሉ ግርማ በ“ከአድማስ ባሻገር” ገጸባሕርያቱን ሲስል እጅጉን ተጠብቦበት እንደነበር ያስታውቃል። የመጀመሪያው ልብወለዱ መሆኑን ስናስታውስ ደግሞ የበለጠ ግሩም ባለሙያነቱን ያሳየናል።
-
“ከአድማስ ባሻገር” (ልብወለድ)
“ማን ነኝ? ምንስ ነኝ? እቃ። ለዚያውም ዋጋ የሌለው የበሰበሰ እቃ። እቃ ሆኜ እንድቀር ያደረገኝ ማንነው? እኔው ራሴ? ወይስ ያፈራኝ ህብረተሰብ? ወይስ አልፌው የመጣሁት የትምህርት አቋም? … እኔ ግን ማንነኝ?”
-
የደራስያኑ ጦርነት
ከመሠረቱ በሥነጥበብ አካባቢ የአስተያየት ግጭት አዲስ ነገር አይደለም። የመናናቅና የመቀናናት ስሜት አለ። የሥነጥበብ ሰዎችም፣ እንደሌላው ሁሉ ደካማ ፍጡሮች ናቸውና … የሥነጽሑፍ ጦርነትም አራጋቢዎችና አስታራቂዎች፣ ዝምተኛ ተመልካቾች፣ ሦስተኛ ኀይል ለመሆን የሚፈልጉ ገለልተኞች አሉበት።
-
ውሎ ከጋሽ ጸጋዬ ጋር
“ ‘ሕይወት ቢራቢሮ’ የተሰኘችው ግጥሜ በጋዜጣ ታትማ በወጣች ማግስት መንግሥቱ ለማ ከቢሮዬ መጥቶ፣ ‘ቢራውን እስቲ አምጣው ወይስ ዝም ብለህ ነው ቢራ ቢሮ ያልከው!’ ብሎ እንደቀለደብኝ ትዝ ይለኛል … አሁን እኮ ደማም ቋንቋ የሚናገር ሰው ሁሉ ጠፋ” ብለው ጋሽ ጸጋዬ ትክዝ አሉ።