“የጉለሌው ሰካራም” (ልብወለድ)

“እንግዲህ መንገደኛው ሁሉ ‘ይህ የማን ቤት ነው?’ ብሎ ሲጠይቅ የተበጀ ሊባል ነው … ‘ተበጀ የትኛው ነው?’ ሲባል ‘ዶሮ ነጋዴው’ ሊባል ነው … ‘ዶሮ ነጋዴው የትኛው ነው?’ ሲባል ‘ያ የጉለሌው ሰካራም’ ሊባል ነው … አወይ! እኔ ተበጀ … ተበላሽቻለሁ!” Continue reading “የጉለሌው ሰካራም” (ልብወለድ)

“መጽሐፈ ጨዋታ” (ቅንጫቢ)

ባባቱ የሚኮራ ሰው ጅል ነው። የሰው አባቱ አንድ አዳም አይደለምን? ሴትን ወንድ አንድ ጊዜ ይደርስባታል መንታ ትወልዳለች። እህልም አንዲት ፍሬ ተዘርታ ብዙ ታፈራለች። ይህ ነገር ከቶ እንዴት ነው? እንጃ ማን ያውቀዋል። Continue reading “መጽሐፈ ጨዋታ” (ቅንጫቢ)

መሰንቆ እና ብትር (ወግ)

አዝማሪ ጣፋጭ በቋረኛው ካሳ ጦር ተማርኳል። ጣፋጭ፣ የደጃች ጎሹ አዝማሪ ስለነበር በብዙ ጦር ሜዳ ላይ ውሏል። ተስፋና ፍርሀት ከፊቱ ተደቅነዋል። ባንድ በኩል፣ አዝማሪን መግደል ነውር የሚያደርገው ባህል ጋሻ ሁኖት ከክፉ እንደሚታደገው ተስፋ ያደርጋል። በሌላ በኩል፣ ደጃዝማች ካሳ ይህን ደምብ ለማክበራቸው እርግጠኛ አይደለም። Continue reading መሰንቆ እና ብትር (ወግ)

“የሺንጋ ቃያ” (ልብወለድ)

ባላ የምሽተታ ኦያት በሰማ ቍጥር ኽይን ይጠውጥን። በኸረም ጭን የምስም ኸማ ኤኽይርፕወ ኸማ እንጐድ ጮዳ ይትጮድ። ኧከሰም ኧከሰም በሜየቴ የትገተረች እርስየ ገረደታ ደንጋኽይታ በፍወረጀታ ይሟሽና … Continue reading “የሺንጋ ቃያ” (ልብወለድ)

“የሺንጋ መንደር” (ልብወለድ)

ባላ የሚስቱን የስቃይ ድምጽ በሰማ ቁጥር ጭንቀት ላይ ይወድቃል። ሆኖም ወንድ ነውና ጭንቀቱ እንዳይታወቅበት አፍኖ ይዞ ሌላ ጨዋታ ያመጣል። አልፎ አልፎም በአጠገቡ የተኛችውን ትንሿ ልጁን ባይበሉባው ጉንጯን ይዳስሳታል … Continue reading “የሺንጋ መንደር” (ልብወለድ)

ማኅደረ ብርሃን – ሀገረ ጃፓን

ቀሚሱን እስከ እግር ጣቱ ሰዶ ወንዱንም ሴቱንም በቶኪዩ ጐዳና ድምቡል ድምቡል ሲል ያሳዩሃል። እንዲህ አስተዋውቀውህ ከቤቱ ሲወስዱህ ተንበርክኮ ይቆይሃል፤ “ንበር ሊለኝ ነው ሊነሳልኝ ነው” ስትል ፍግም ብሎ መሬት ይስምልሃል። አደግድግ አንተም … እንዳገርህ ‘ክበር ተከባበር’ ነውና እጅ ንሳ። Continue reading ማኅደረ ብርሃን – ሀገረ ጃፓን

የጃፓን ባህል ቅኝት

የካቲት 3 ቀን በጃፓን የክረምት ማጋመሻ በዓል ይባላል። በዚህም በዓል ቤተ ዘመዱ ሁሉ በየቤቱ እየተሰበሰበ ቆሎ እየተቆላ ‘ሰይጣንና ክፉ ነገር ውጣ … ሲሳይና ጤና ወደ ቤት ግባ’ እያለ ቆሎውን እየዘገነ ይበትናል፤ የተረፈውንም ይበሉታል። ይኸውም ባገራችን በኢትዮጵያ በየባላገሩ ለእንቁጣጣሽና ለግንቦት ልደታ እንደሚደረገው ነው። Continue reading የጃፓን ባህል ቅኝት