-
አፈወርቅ ተክሌ እና “ቪላ አልፋ”
እንዲህ የመሰለውን መኖሪያ ቤት ለመሥራት ምን እንዳሳሰበው እንዲነግረኝ አፈወርቅን ጠይቄው ነበር። ለማናገር ፈቃደኛ ቢሆንም … አናጢዎቹ በየደቂቃው ይጠሩታል … ገና ተመልሶ ቁጭ ከማለቱም ቀለም ቀቢዎች ይጠሩታል።
-
ዳኛቸው ወርቁና መጽሐፎቹ
“መጀመሪያ በአምስት ብር ነበር የሚሸጠው። ነገር ግን አልሄድ ስላለ አስር ብር አደረግሁት። አሁንም እንደገና አልሄድ አለ። ስለዚህ መሸጫ ዋጋውን አስራ አምስት ብር አድርጌዋለሁ” አለኝ። ይህንን ስሰማ ሳቅ ወጥሮ ያዘኝ። ነገር ግን ዳኛቸውን እንዳላስቀይመው በመፍራት ሳቄን ታግዬ አስቀረሁት።
-
“በራሪ ወፎች” (የሥዕል እይታ)
የስናፍቅሽ የአሳሳል ጥንካሬ በ“ቅርጻዊ” ስልት ሸራዋን ማድመቅ እንደሆነ ግልጽ ነው። መስመሮቿን በሚገባ ትስላለች። ቀለሞቿን ደግሞ አነባብራ ትጠቀማለች። ሰፋ ያለ ምሕዋር መፍጠርንም የግሏ አድርጋዋለች።
-
ስለ ኢትዮጵያ ደራስያን
ይሁን እንጅ ኢትዮጵያዊ የሆነ አሳብ፣ ኢትዮጵያዊ በሆነ ንግግር የመግለጹ ዕድል ለግዕዝ ቀርቶበት ለአማርኛ ሆኗል። አማርኛው ዛሬ ዘመን የማንናገርበትና የማንጽፈው፣ ለማስተዋሉም የሚያስቸግረንና የሰዋስው አካሔዱ የተለዋወጠ ብዙ ቃልና አገባብ አለበት።
-
የግዕዝ ሊቃውንት እና አዲሱ ዘመን
የኢትዮጵያን የጥንቱን ትምህርት ከሚያውቁት ሊቃውንት አማርኛንና ግዕዝን ለማጣራት፣ ያለቃ ኪዳነ ወልድን ያህል የሚደክም ብዙ አልተገኘም።
-
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ
አማርኛ ማሠሪያ አንቀጹን አርቆ፤ ከማህሉ ልዩ ልዩ አሳብ ጣልቃ ማግባት የተፈጥሮ ጠባዩ ነው ብለናል። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ይህን ሳይከተሉ ንግግሩን ባጭር ባጭሩ ማሠር ልዩ ባሕርያቸው ነው። አንዳንድ ሰው ብላቴን ጌታ ኅሩይ አማርኛን በውጭ አገር ንግግር እንጂ በተፈጥሮ ጠባዩ አያስኬዱትም ብሎ ጽፎባቸዋል።
-
ማቲክ ኬዎርኮፍ – አርመኑ ነጋዴ
ኬዎርኮፍ ከአጎቱ ጋር በመሆን ከጅቡቲ ትንባሆ ወደ ፈረሳይ ሐገር በመላክ ትልቅ ንግድ ጀመሩ። ቀስ እያለም ንግዱን ወደ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ እና አዲስ አበባ አስፋፋ። ጎራዴ፣ ሰይፍ፣ ጩቤ እና የመሳሰሉትን በ1890ዎቹ በሐረር ያመርት እንደነበር አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
-
የ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ደራሲዎች
በጅሮንድ ተክለሐዋርያት ፍጹም አማርኛ በሆነ ግጥም ጥቂት ተረት ጽፈው ካሳተሙና በተረት ዓይነት ቲያትር ከጻፉ በኋላ፣ አሁንም ንጹሕ በሆነ አማርኛ ስለ እርሻ ትምህርት ጽፈዋል።
-
የፒያሳው ኬዎርኮፍ ሕንጻ
በሚያዝያ 1928 መጨረሻ ላይ የአዲስ አበባ ሕዝብ አራዳን መዝረፍ እና ማውደም ጀመረ። የኬዎርኮፍ ሱቅም ይህ እጣ አልቀረለትምና ከአካባቢው ሕንጻዎች ጋር ተቃጥሎ በአጥንቱ ቀረ። በአሁኑ ጊዜ ይህ ህንጻ ሮያል ኮሌጅን፣ አቢሲኒያ ባንክን እና ካስቴሊ ሬስቶራንትን በውስጡ ያስተናግዳል።
-
“በዕውቀቱ ሥዩም” (ቃለመጠይቅ)
ወደ ሥነጽሑፍ ከመግባቴ በፊት ሥዕል እሞክር ነበር። ሥዕሎቹ ለግጥሞቹ ወይም ለታሪኩ እንደ ማስረጃ ወይንም ምትክ እንዲሆኑ ብዬ አይደለም። በራሳቸው መንገድ እንደ ቅኔ እንደ ሀሳብ እንዲታዩ ነው።